የትምህርት ቤቶች መዘጋት እና ማዋሃድ የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎች
Summary : የትምህርት ቤቶች መዘጋት እና ማዋሃድ የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎች
የትምህርት ቤቶች መዘጋት እና ማዋሃድ የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎች
ውድ የ ቤተሰቦች፣
ትናንት ማታ፣የትምህርት ቦርድ ስብሰባ አካይደን ነበር፣እና የተወሰኑ አንዳንድ ቁልፍ ዝመናዎችን ላጋራቹ ነው።
ከNorth Beach፣ከSanislo፣ከSacajawea እና፣ከStevens አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ማህበረሰብ ሊካሄድ ታስቦ የነበረውን የመስመር ላይ የማህበረሰብ ስብሰባዎች ተሰርዟል።ይህን ያደረግነው ቦርዱ ሁላችንም የምንወዳቸው ቤተሰቦች ጠቃሚ ግብአትን መሠረት በማድረግ በታህሳስ ወር ስለ የትምህርት ቤቶች መዘጋት እና ማዋሃድ አስመልክቶ የማህበረሰቦች ድምፅ ለመስማት ታስቦ የነበረውን እቅድ እንዲዘገይ በመወሰኑ ነው።በዚህም ምክንያት፣ስለ ትምህርት ቤቶች መዘጋት እና ማዋሃድ የሚለውን የመጀመርያ ምክረ ሃሳብ ለመተው እያሰብኩ ነው።
ቀጣዩ እርምጃችን- ለቀጣይ እቅድ ከትምህርት ቦርድ ጋር በመቀመጥ መወያየት ይሆናል።ከእነዚህ ውይይቶች በፊትም ሆነ በውይይቱ ወቅት በአሁኑ ጊዜ የማህበረሰብ ስብሰባዎች ማድረግ ፍትሃዊ አይሆንም።
እስከ አሁን እንደ ማህበረሰብ ካደረግናቸው በጣም ከባድ ውይይቶች አንዱ ስለ የትምህርት ቤቶች መዝጋት እና ማዋሃድ ነው።ከተጎዱት የትምህርት ቤት ቤተሰቦች፣ከትልቅ የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ማህበረሰብ፣ ከሰራተኞቻችን እና የትምህርት ቦርድ ጋር የተደረገው ውይይት ውጤታማ እና አንዳንዴም የሚያም ነበር።ማንም የሚወደው ትምህርት ቤት እንዲዘጋ እንደማይፈልግ እንረዳለን፡፡እና እርስዎ ትምህርት ቤትዎ፣መምህራንዎ፣ሰራተኞች እና እያንዳንዱን ተማሪ እንዲያድግ የሚረዳውን ባህል ምን ያህል እንደሚወዱ እናደንቃለን።
የበጀት ክፍተታችንን ለመቅረፍ እና ቀጣይነት ያለው ስርዓት ለመገንባት ስንሰራ እያንዳንዱ ተማሪ እንዲበለፅግ አስተያየት ለሰጡን የትምህርት ቤታችን ማህበረሰቦች ማመስገን እፈልጋለሁ።
ከትብብር ጋር፣
ዶክተር ብሬንት ጆንስ
ዋና ሃላፊ
ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች